The Rising South podcast artwork

The Rising South

by ወሰንሰገድ አሰፋ · EN · Society & Culture

የዓለም አቀፍ የኃይል ሚዛን እየተቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት - ኢትዮጵያን፣ አፍሪካን እና ሌሎችን የሚቀርጹ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ሃይሎች ወደምንመለከትበት ወደ “ራይዚንግ ሳዉዝ” እንኳን በደህና መጡ፡፡ ደቡባዊ አመለካከቶችን ወደ ዓለም አቀፋዊ ውይይት መድረክ ስናቀርብ የአሰላሳዮችን ፣ የመሪዎችን እና የለዉጥ ፈጣሪዎችን ሃሳብ ያድምጡ።

141episodes
2025first episode
Severalepisodes a week
1 h 0 mintypical episode

Latest episodes

  1. የአፍሪካ ቀንድ በባለብዙ-ዋልታ ዓለም፦ የጂኦፖለቲካ የስበት ማዕከልነትና ሉዓላዊ ውሳኔ

    "አፍሪካውያን የራሳቸውን ውሳኔ በራሳቸው የመወሰን ስትራቴጂካዊ ነፃነት ሊኖራቸው የሚችለው ለራሳቸው የሰላምና የልማት ጥረቶች የገንዘብ አስተዋፅኦ ማድረግ ሲችሉ ብቻ ነው። በውጭ ፋይናንስ ላይ ጥገኛ ከሆንክ የሀሳብህ ባለቤት መሆን አትችልም።" ሲሉ...

    1 h 0 min
  2. ከመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት እስከ አህጉራዊ ደህንነት፦ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እንዴት ለአፍሪካ መከታ ሆነ?

    በዚህኛው የራይዚንግ ሳውዝ ዝግጅታችን በክፍል አንድ በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ግጭት፣በቀይ ባህር አቅራቢያ የሚታየው የውጭ ኃይሎች ወታደራዊ መገኘት እና የባህርላይ የንግድ መስመሮች መስተጓጎል በምስራቅ አፍሪካ ኢኮኖሚና ደህንነት ላይ...

    1 h 0 min
  3. የስፔስ ቴክኖሎጂ፡ የአፍሪካ ስትራቴጂካዊና መጻኢ እድል

    "የስፔስ ቴክኖሎጂ እዚሁ ቤታችን ነው፣ አጠገባችን ነው ያለው። ግብርናችን ጋር አለ። የምንሳፈርበት ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ አለ። የስፔስ ቴክኖሎጂ ያልገባበት ቦታ የለም።... ያለ ስፔስ ቴክኖሎጂ ወደፊት መሄድ አንችልም ማለት ነው።... ስለዚህ...

    1 h 0 min
  4. ከነዳጅ ጥገኝነት ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል፤ ከባለአንድ ወገን ተፅዕኖ ወደ ብሪክስ ቤተሰብ

    "ከባድ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቴክኖሎጂን ከመሞከር ወጥተን ወደ ሥርዓታዊ ኢኮኖሚ መሸጋገራችንን ያሳያሉ። በአገራችን ከ60% እስከ 70% የሚሆነውን የምርትና አገልግሎት እንቅስቃሴ የሚይዙት እነዚህ በመሆናቸው፣ ሽግግሩን ስኬታማ ለማድረግ...

    1 h 0 min
  5. የስነ-ጽሁፍ ሚና በማንነት እና በታሪክ ንቃተ-ህሊና ግንባታ

    "ወደ ዘመናዊ ስነጽሁፍ ስንመጣ ዘመናዊ ስነጽሁፍ በአብዛኛው በቴክኒኩ የውጪውን ፈለግ የተከተለ ስለሆነ ኢትዮጵያዊነት አሻራን በቴክኒኩ ላይ ማግኘት ያስቸግራል፤ ያው በጭብጡ ወጣም ወረደ ኢትዮጵያዊ ባህል ነው፣ ኢትዮጵያዊ ማንነት ነው። ... በዚህ...

    1 h 0 min
  6. የባዮ-ኮሎኒያሊዝም ወጥመዶች እና የአፍሪካ ወጣቶች የሳይንስ ሉዓላዊነት

    ''ዩኤስኤአይዲ (USAID) ከተዘጋ በኋላ ይፋ የሆኑት አዳዲስ የሁለትዮሽ የጤና ስምምነቶች፣ የአፍሪካ ሀገራት የህዝብ ጤና መረጃዎቻቸውን እና የዘረመል (ጄኔቲክ) ሀብቶቻቸውን ለውጭ አካላት ሙሉ በሙሉ አሳልፈው እንዲሰጡ የሚያስገድዱ እና ፈቃደኛ...

    1 h 0 min
  7. የመካከለኛው ምሥራቅ ቀውስ እና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ስጋት

    "አሁን በዋነኝነት የጨመረው ነገር የኢንሹራንስ አረቦን ፣ የሴኩዩሪቲ ክፍያ እና የመሳሰሉት ናቸው... ከዚህ በፊት ሲከፈል የነበረውን ያህል ዋጋ መቶ ፐርሰንት በሚባል ደረጃ እጥፍ ሆኗል። ያ ደግሞ በተዘዋዋሪ የመጨረሻ ያለቀው መድሃኒት ላይ ዋጋ...

    1 h 0 min
  8. ከአእምሮአዊ ጥገኝነት ወደ አፍሪካዊ ሉዓላዊነት፦ የበርሊን ጉባኤን ጥቁር ጥላ ማጥፋት

    “በግድግዳው ላይ የተሰነጠቁ ስንጥቆችን ለማከም ሲሚንቶ ለጥፈን ለማስተካከል እንሞክር ይሆናል፤ ነገር ግን ዋናው ችግር ያለው በሕንጻው መሠረት ላይ ነው። … ወደፊት ወዴት እየሄድን እንዳለን ለመረዳት፣ ይህ የበርሊን ጉባኤ መርዝ አእምሮአዊ እንደሆነ...

    1 h 0 min
  9. ከእውቀት ተጠቃሚነት ወደ እውቀት አምራችነት፦ የአፍሪካ ትምህርት ሥርዓት የወደፊት ጉዞ

    “ችግሩ የአፍሪካውያን የአእምሮ ወይም የፈጠራ አቅም ማነስ አይደለም፤ በፈጠራችን የበለፀግን ነን። ዋናው ተደቅኖብን ያለው ፈተና የትምህርትና የምርምር ሥርዓታችን ታሪክ አጋጣሚ ሆኖ ለአዲስ ፈጠራ ይልቅ ለእውቀት ማስተላለፍ ብቻ ተቀርጾ መቆየቱ ነው።”...

    1 h 0 min
  10. የአፍሪካ ሉዓላዊነት በፖሊሲ ነጻነት እና በጤናው ዘርፍ

    "አፍሪካውያን መሪዎች በመጨረሻ ተጠያቂ መሆን ያለባቸው ለማን ነው? ለገዛ ዜጎቻቸው ወይስ ለውጭ አጋሮቻቸው? መንግሥታት ለውጭ የፖሊሲ መመሪያዎች፣ ለገንዘብ ድጋፎች ወይም ለአለም አቀፍ ተቀባይነት ቅድሚያ ሲሰጡ፤ የገዛ ዜጎቻቸውን የዕለት ተዕለት...

    1 h 0 min
  11. የአፍሪካን የእንስሳት ሀብት ማዘመን፡- ከምርታማነት እስከ አህጉራዊ እሴት ሰንሰለት

    "እኛ የምንፈልገው የተቀናጀ አህጉራዊ የእንስሳት ሀብት እሴት ሰንሰለትን መፍጠር ነው። ከአምራቹ ጀምሮ እስከ እሴት መጨመር እና ማቀነባበር ድረስ ያሉትን ሂደቶች በሙሉ በመደገፍ፤ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የስጋ እና የወተት ምርቶችን በራሳችን አህጉር...

    1 h 0 min
  12. ምርምር ለአፍሪካ ኢኮኖሚ እድገት፦ ያልተነካው እምቅ አቅም

    "ምርምርን በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ውስን ሀብት ባለባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ለልማት 'የአቅም ማባዣ' (force multiplier) አድርጌ እገልጸዋለሁ። ሀብት ውስን በሚሆንበት ጊዜ ዋናው ፈተና የሀብቱ እጥረት ሳይሆን ያንን ያለውን ሀብት ምን...

    1 h 0 min
  13. ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሀብት ፈጣሪነት፦ የአፍሪካ ትምህርት ሥርዓትና የዕውቀት ነጻነት

    "የትምህርት ሥርዓታችን አሁንም ድረስ የራሳቸውን ሀብት የሚፈጥሩ ሉዓላዊ ዜጎችን ከመቅረጽ ይልቅ በሌሎች ላይ ጥገኞች የሆኑ የሥራ ፈላጊዎችን ስብስብ እያመረተ ይገኛል።... እውነተኛ ነጻነት የሚጀምረው የአፍሪካን የአገሬው ተወላጅ ዕውቀቶች እና...

    1 h 0 min
  14. ከአፍሪካ ሉዓላዊነት እስከ ባለብዙ-ዋልታ ዓለም

    "ይህ (በሀገር ውስጥ ምንዛሬ የመገበያየት ሞዴል) አገሮችን በፋይናንስ ማዕቀብ ከሚያስረው ስዊፍት [Swift] የክፍያ ስርዓት ለመውጣት ጥሩና ውጤታማ መንገድ ነው ብዬ አምናለሁ። ይህ ሞዴል የደቡባዊው ንፍቀ ክበብ ሀብት በምዕራባውያን ኃይሎች እጅ...

    1 h 0 min
  15. ከጂኦፖለቲካ እስከ ጤና ስርዓት፤ የአፍሪካ ሉዓላዊነት ጉዞ

    "ቻይናውያን በታሪካቸው... መሬት ለመቀማት ወታደራዊ ካምፖችን ወይም ሰፈሮችን ለመመስረት አልመጡም። ይህንን ያደረገው አንድ የወራሪዎች ቡድን ብቻ ነው—በተለይም እንግሊዞች፤ አሁን ደግሞ አሜሪካውያን ይህንን የብሪታንያን ባህሪ ወርሰውታል።" ሲሉ...

    1 h 0 min
  16. ከመረጃ-መር ፖሊሲ እስከ ሀገር በቀል ምርት፤ የአፍሪካ የኢኮኖሚ ትንሳኤ

    "የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችና አገልግሎቶችን በተመለከተ በህዝቡ ግንዛቤ ላይ ጠንክሮ መስራት ይኖርበታል። የራሳችንን መለያ (Brand) ውብ ካደረግነው፣ የእኛ ምርት በአለም አቀፍ ገበያ ምርጡ መሆን ይችላል። ሁሉንም ነገር መጀመር...

    1 h 0 min
  17. ከተውሶ መዋቅር ወደ ሉዓላዊ ማዕቀፍ፡ የአፍሪካ ትምህርት ሥርዓት ዳግም ቅርጻ

    "አፍሪካ የራሷን የአእምሮ ነጻነት ማረጋገጥ ካለባት፣ የትምህርት ሥርዓቱ በሌላ ሀገር በተቀረጸ የተውሶ መዋቅር ላይ ሳይሆን፣ በራሷ ነባራዊ እውነታዎችና ምኞቶች ላይ የተመሠረተ ሉዓላዊ ማዕቀፍ ሆኖ እንደገና መነደፍ አለበት። የአፍሪካን አእምሮ ነጻ...

    1 h 0 min
  18. ከረግረጋማ መሬት ኢኮኖሚ እስከ ቡና ወጪ ንግድ ስኬት

    "የመንግስት ፖሊሲ በግብርናው ዘርፍ በጎን ከመስፋፋት ይልቅ የተጠናከረ (ምርታማ) ግብርናን መጠቀም አለብን የሚል ነው። የዚህ ግብርና በጎን መስፋፋት ተፅዕኖ ረግረጋማ መሬቶቻችንን በከፍተኛ ሁኔታ እና ከመጠን በላይ እንዲራቆቱ ያደርጋል። ስለዚህ...

    1 h 0 min
  19. ከአእምሮ ነፃነት እስከ አህጉራዊ የውኃ ሀብት ሉዓላዊነት

    "የአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የእውቀት ምርትን፣ ታሪካዊ ትውስታን እና ምሁራዊ ነፃነትን መልሶ ከመያዝ ትግል ጋር በቀጥታ የተገናኘ ነው። የትምህርት ሥርዓቶቻችን እና የታሪክ ትረካዎቻችን ከአሮጌው የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ነፃ ካልወጡ አህጉሪቱ...

    1 h 0 min
  20. የምዕራባውያን በበላይነት የተቆጣጠሯቸው የፋይናንስ ተቋማት እና የአዲሱ ዓለም ሥርዓት ፈተናዎች

    “በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓቶች ላይ የተዘረጋው የምዕራባውያን የበላይነት የሚቀጥለው በተቋማዊ የበላይነት ቅንጅት አማካኝነት ነው። ይህም እንደ የአሜሪካ ዶላር ያሉ የመጠባበቂያ ገንዘቦች ካላቸው መዋቅራዊ ኃይል እና ከዓለም አቀፍ የክፍያ ስልቶች...

    1 h 0 min

Showing the latest 20 of 141. Every episode is in the API: GET /v1/podcasts/pod_51zx2r5ef4ans8kxmc2g16dpxa/episodes

More society & culture podcasts →